ህዳር 7 ቀን 2015 ዓ.ም (ወዩ ህዝብ ግንኙነት)
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ በጦርነት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን የቦሩ ሜዳ ት/ቤት መልሶ ለማቋቋም ስፔን ካታላን ከሚገኘው GAVA MAR ት/ቤት ጋር አለም አቀፍ ግንኙነት በመፍጠር ድጋፍ ለማድረግ እየሰራ ነው።
ዩኒቨርሲቲው ከGAVA MAR ት/ቤት ጋር በመተባበር የሚሰራውን ስራ በቦሩ ሜዳ ት/ቤት በመገኘት የመጀመሪያ ውይይቱን በተወካዩ በኩል አካሄዷል።
ይህንኑ በተመለከተ በነገው እለት የETHIO – GAVA ተወካይ ስፔን ካታላን ከሚገኘው GAVA MAR ት/ቤት ሀላፊዎችና ተማሪዎች ጋር ቀጥተኛ የቪድዮ ኮንፍረንስ የሚያካሄድ ይሆናል።
የACCEeDE ድርጅት ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከሚሰራቸው የማህበረሰብ አገልግሎቶች መካከል አንዱ የሆነውን የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ልማት ላይ በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ እያዘጋጀ ይገኛል። የሚያስችል የስምምነት ሰነድ እያዘጋጀ ይገኛል።