የአፕ ፋክተሪ አካዳሚ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከማይክሮ ሶፍት እና ደመራ ጋር በመተባበር ለስድስት ወራት የሚቆየው የሶፍት ዌር ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡

በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶክተር መላኩ ታመነ ፕሮግራሙ እውን እንዲሆን አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና በመስጠት ወሎ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ካሉት አስራ አምስት የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ በመሆኑ እንዲህ አይነት ፕሮግራም ለተልዕኮው መሳካት ቀጥተኛ ምላሽ ይሰጣል ብለዋል፡፡

ስልጠናው በሶፍት ዌር ልማት ዘርፉ የሚያበረክተው ድርሻ ጉልህ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር መላኩ ካሁን ቀደም በአካዳሚው የተሳተፉ ሰልጣኞች በመስኩ ያላቸው አበርክቶ የዚህ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በደመራ ቡድን የተዘጋጀው ይህ ስልጠና የኢንዱስትሪዎችን ችግር ለመፍታት ያግዛል ያሉት ዶ/ር መላኩ ሰልጣኞች በመስኩ አገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ገብያውን ሰብሮ ለመግባት በቂ ክህሎት እንደሚጨብጡ ያላቸውን እምነት ገልጸው ለዚህ ዩኒቨርሲቲው ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል ብለዋል፡፡

ዶ/ር መላኩ ሰልጣኞች በጽኑ ፍላጎት፣ ቁርጠኝነት እና ጥረት አለማቸውን ሊያሳኩ እንደሚገባ በማሳሰብ ደመራ በዘርፍ ሰልጣኞችን ለማብቃት ለሚያደርገው ጥረት ምስጋና ችረዋል፡፡

የደመራ ድርጅት መስራች የሆኑት የተመኝ ከበደ በበኩላቸው ይህን ፕሮግራም ለመሳተፍ ተወዳድረው እድል ላገኙ ሰልጣኞች የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ስለ ደመራ አመሰራረት እና አላማ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የቡድን አባላቶቻቸውም ለሰልጣኞች ገለጻ አድርገዋል፡፡

4/06/2106

Scroll to Top