ወሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ወረዳና ከተሞች የሚገኙ እንሰሳትን ጤና ለማሻሻል የክትባትና የህክምና አገልግሎት ሰጠ።

ጥር 7/2016 ዓ ም (ወሎ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጽ/ቤት)

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የእንሰሳት ህክምና ት/ቤት በደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ኩታበር፣ኩታበር፣ ደሴ ዙሪያና ሀይቅ የሚገኙ የቤት እንሰሶችን ጤና ለመጠበቅ የክትባትና የህክምና አገልግሎት ሰጥቷል።

የተሰጠው ክትባትና የህክምና አገልግሎት ለቀንድ ከብት፣ለጋማ እንሰሳት፣ ለፍየሎች፣ ለበጎችና ውሾች ነው።

ዩኒቨርሲቲው የሰጠውን ክትባትና የህክምና አገልግሎት አስመልክተው መረጃ የሰጡን የእንሰሳት ህክምና ት/ቤት የድህረ ምረቃ፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪ ዶ/ር ሰላማዊት ፋንታሁን የተሰጠው ክትባት በደሴና ኮምቦልቻ እየታየ ያለውን የውሻ በሽታ ምልክት በቀላሉ መፍትሄ ለመስጠት ያስችላል ብለዋል።

አያይዘውም ዶ/ር ሰላማዊት ዩኒቨርሲቲው ክትባቱን የተሰጠው ባለቤት ላላቸው ውሾች በመሆኑ የውሻ በሽታ በዘላቂነት ለመከላከል ባለቤት የሌላቸውን ውሾች የማስወገድ ስራ ሊሰራ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።

ውሾችን ሲያስከትቡ ያነጋገርናቸው የደሴና ኮምቦልቻ ከተማ ኗሪዎች ወሎ ዩኒቨርሲቲ የውሻ በሽታ እንዳይከሰት የቅድመ መከላከል ክትባት መስጠቱ ከስጋት ነጻ ያደረጋቸው ቢሆንም ባለቤት የሌላቸው ውሾች ላይ መፍትሄ ሊወሰድ ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ3 ሺ በላይ ሰዎች በውሻ በሽታ የሚጎዱ ሲሆን ወሎ ዩኒቨርሲቲው የውሻ በሽታን ለመከላከል የሚያስችል ክትባት በየዓመቱ እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል።

Scroll to Top