On March 1, 2024, Wollo University hosted a training session focused on data analysis, catering to researchers across diverse fields. The primary objective of this session was to bolster participants’ proficiency in software-based, paper-free data analysis techniques, thereby augmenting their research acumen and capabilities.
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለተመራማሪና ባለሙያዎች በመረጃ ትንተና ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ።
=====================================================
የካቲት 22/2016 ዓ ም ( ወሎ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጽ/ቤት)
በወሎ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተመራማሪና ባለሙያዎች ከወረቀት በነጻ መልኩ በኦን ላይን የመረጃ ትንተና እንዲያካሄዱ የሚያስችል የሶፍት ዌር ስልጠና ተሰጥቷል።
በዚህ የሶፍት ዌር ስልጠና ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ዳይሬክተር ብርሀን አስማሜ (ዶ/ር) ስልጠናው በወሎ ዩኒቨርሲቲና በGIz ትብብር የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው ሰልጣኞች የተሻለ የመረጃ ትንተና ክህሎት እንዲኖራቸው ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል።
የዚህ ስልጠና አስተባባሪ እና አሰልጣኝ ዶ/ር የሽመቤት አሊ በበኩላቸው ስልጠናው ተመራማሪዎች ሶፍት ዌርን ተጠቅመው መረጃዎችን እንዴት ማደረጀትና መተንተን እንዳለባቸው በቂ ግንዛቤ የምንፈጥርበት ነው ብለዋል።
ይህም የሶፍት ዌር የመረጃ ትንተና ስልጠና በቀጣይ ስልጠናውን ላልወሰዱ ተመራማሪዎች የሚሰጥ እንደሆነ ከአሰልጣኞች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።