ወሎ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻሊስት የህክምና ባለሙያዎችን አስመረቀ


ወሎ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት አራት አመታት የሪዚደንት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 11 የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና እና 9 የማህጸንና ጽንስ ህክምና ስፔሻሊቲ ሀኪሞችን አስመርቋል።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርትና አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር መንግስቱ ወርቁ ሪፖርት አቅርበዋል። በትምህርት ቤቱ በስፔሻሊቲ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ከቆዩ ተማሪዎች መካከል የመጨረሻ ፈተናቸውን በብቃት ያጠናቀቁ 20 የስፔሻሊቲ ተማሪዎች መመረቃቸው በሪፖርቱ ተገልጿል።

በዚህ የምርቃት ፕሮግራም ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ተወካይ እና የሬጅስትራርና እና አልሙናይ ዳይሬክተር ዶ/ር ገዛኸኝ አሰፋ ለተመራቂዎች የስራ መመሪያ ሰጥተዋል። ተመራቂዎች በሄዱበት ሁሉ የዩኒቨርሲቲው አምባሳደር ሆነው እንዲሰሩም ከመልካም ምኞት ጋር አደራ ተሰጥቷቸዋል።

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የልዕለ ህክምና ካምፓስ ተወካይ ችፍ ኤክስኪዮቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር መታደል አዳነ ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልክት አስተላልፈዋል፤ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ለመጡት ተጋባዥ ፈታኝ ሲኔር ሐኪሞችም ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

ህክምና ጤናን በመጠበቅ እና በማከም ከፈጣሪ በታች የሰው ልጅ ህይወት ዋስትና ነው። በመሆኑም ተመራቂ ስፔሻሊስት ሃኪሞች የሀገሪቷ የጤና ዘርፍ ላይ የሚኖራቸው ሚና ጉልህ ነው። ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ!!!

Scroll to Top