ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር የትብብር መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተጠሪ ከሆነው እና በስሩ ሌሎች እንዱስትሪዎችን ከሚያስተዳድረው ከአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።
የመግባቢያ ሰንዱ በዋናነት በጋራ ምርምር ስራዎች፤ በመምህራን እና ተማሪዎች የስራ ላይ ልምምድ (Internship and Externship Activities)፣ በሃብት መጋራት፣ በስልጠና፣ በስርዓተ ትምህርትቶች ቀረጻ እና በመሳሰሉት ዘርፎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
ስምምነቱን የተፈራረሙት በወሎ ዩኒቨርሲቲ በኩል የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሃዋ ወሌ ሲሆኑ የኢንዱስትሪ ትስስር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር ዶ/ር አሳምን አያሌው ስለ ወሎ ዩኒቨርሲቲ የስራ እንቅስቃሴዎች እና አጠቃላይ ሁኔታ በፕሮግራሙ ላይ ገለጻ አቅርበዋል።


