በወሎ ዩኒቨርሲቲ የደሴ፣ የኮምቦልቻ እና የጢጣ ግቢ ከፍተኛ፣ መካከለኛ እና የታች የስራ መሪዎች መካከል የጋራ ውይይት ተካሂዷል። የውይይቱ ተሳታፊዎች ፕሬዝዳንቱ እና ም/ፕሬዝዳንቶች፣ ዲኖች፣ ዳይሬክተሮች እና የትምህርት ክፍል ተጠሪዎች ናቸው።
በባለሙያዎች የቀረቡ እና ውይይት የተደረገባቸው ሃሳቦች HEMIS (Higher Education Management Information System), Program Evaluation, Self Assessment Studies Report, and Draft Legislation Report የሚሉ ናቸው።
ከነዚህ የውይይት ሃሳቦች መቅረብ አስቀድሞ ዩኒቨርሲቲው የአካ/ገዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር አወል ሰይድ በጅግጅጋ ከተማ የተካሄደውን 32ኛውን የከፍተኛ ትምህርት ጉባኤ የውይይት ውጤቶችን አስመልክቶ ማብራሪያ አቅርበዋል።
የንግግረቸው ትኩረት የነበረው ወሎ ዩኒቨርሲቲ Applied Univrsity ከመሆኑ አንጻር ትኩረት አድርጎ ሊሰራባቸው የሚገባውን እና ወደራስ ገዝ የኒቨርሲቲ ለመሸጋገር በሚያስችለው ነጥቦች ዙሪያ ነበር። ም/ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ሁሉም የዩኒቨርሲቲው የስራ መሪ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ አሳስበዋል።
HEMIS (Higher Education Management Information Systemን በተመለከተ የዩኒቨርሲቲው የፕላንና በጀት ዳይሬክተር አቶ አበባው ደምሴ እና የክፍሉ ባለሙያ አቶ ሙህድን ዓሊ HEMISን በተመለከተ ማብራሪያ እና ስራው ያለበትን ደረጃ አቅርበዋል።
የ Program Evaluationን በተመለከተ ስለአስፈላጊነቱ እና እንዴት መሰራት እንዳለበት ዶ/ር ዓሊ ያሲን፣ የትምህርት ጥራት ዳይሬክተር፣ ማብራሪያ ካቀረቡ በኋላ በኮምቦልቻ ግቢ የተሰሩ 3 የውስጥ የትምህርት ኦዲት ሪፖርቶች እንዲቀርቡ አድርገዋል። አቅርቦቱ ለሌሎች ትምህርት ክፍሎች እና ኮሌጆች እንደልምድ እንዲሆን ታስቦ ነው።
ሌላው በእለቱ ውይይት የቀረበው የዩኒቨርሲቲውን ደንብ (Legislation)ማሻሻል አስመልክቶ ነው። የዩኒቨርሲቲው ደንብ ዩኒቨርሲቲው ካለበት ወቅታዊ አቋም እና ከተሰጠው ተልዕኮ አንጻር (Applied University)ማሻሻል በማስፈለጉ ቀደም ብሎ በተቋቋመወ ቡድን ሲሰራ ቆይቷል። በዚሁ መሰረት ቡድኑ ማሻሻያና ጭማሪ ያደረገባቸውን ልዩ ልዩ አንቀጾች ከነማሻሻያቸው በሪፖርት መልክ በዶ/ር አስረሴ ሞላ በኩል ቀርቧል።
ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ደሴ ላይ Convention and Exhibition Center የማቋምን አስፈላጊነት በተመለከተ የመነሻ ሃሳብ ቀርቧል። ሃሳቡ የቀረበው በኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ተቋም የአርክቴክቸር መምህራን በኩል ነው። ማዕከሉ ቢቋቋም ምርምሮች፣ ሴሚናሮች፣ ስብሰባዎች፣ ኤግዚቢሽኖች እና የባህል ፌስቲቫል ወዘተ. ሊካሄዱበት እንደሚችል፣ ደሴ ከተማን የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከል ማድረግ እንደሚያስችልና ገቢን ማመንጨት እንደሚያስችል የሃሳቡ አመንጭዎች ገልጸዋል። የቀረበው ሃሳብ ዋና አላማ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ለማሳሰብና የቤት ስራውን ለመስጠት እንደሆነ ተገልጿል።
በመጨረሻም በዶ/ር መንገሻ አየነ (የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት) አወያይነት ከላይ በቀረቡት የውይይት መነሻ ሃሳቦች ላይ ሳታፊዎች አጠቃላይ አስተያየቶችን፣ ጥያቄዎችን እና ማሻሻያዎችን የተሰጡ ሲሆን ዶ/ር መንገሻም በዋና ዋና ነጥቦች ላይ በማጠቃለያ መልክ ሃሳባቸውን አጋርተዋል።