ወሎ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ከግብርና ኮሌጅ ጋር በመተባበር በኮሌጁ በተለያዩ የስራ ክፍሎች በተለያዩ ሃላፊነት ቦታ ላይ ለሚገኙ አካላት በመሪነት ክህሎት ዙሪያ ለሶስት ቀናት ስልጠና ሰጥቷል።
በቢዝነስ እና ማኔጅመንት ኮሌጅ የማኔጅመንት ት/ክፍል ሃላፊ እና አሰልጣኝ ዶ/ር መንግስቱ ጉልቲ ስልጠናው ተግባቦት፣ ውሳኔ አሰጣጥ፣ ችግር አፈታት፣ ዘመኑን የዋጁ የመሪነት ጥበብ እና ክህሎት የሚሉ አንኳር ጉዳዮችን ያካተተ መሆኑን ገልጸው ስልጠናው የአመራርነትን አቅም ለማጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።
ስልጠናው ዶ/ር መንግስቱን ጨምሮ የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን በሆኑት ዶ/ር ይመር አያሌው እና ከማኔጅመንት ት/ ክፍል መምህርት ዘሙ መሀመድ የተሰጠ ሲሆን በስልጠናው ማጠቃለያ ከተሳታፊዎች ለተሰነዘሩ አስተያየቶች መልስ የሰጡት ዶ/ር ይመር ስልጠናው በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።