ወሎ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም የደሴ እና የልዕለ ህክምና ግቢ አጠቃላይ ሰራተኞች በተገኙበት የ2018 ዓ.ም የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም አመላካቾች (Key Performance Indicators – KPI) የትኩረት አቅጣጫ ላይ በደሴ ግቢ ውይይት አደረገ።
በመርኃ-ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አወል ሰኢድ ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም በሃገር አቀፍ ደረጃ ያወረዳቸውን የKPI ተግባራትን መሰረት በማድረግ ከመማር ማስተማር፣ ከምርምር፣ ከማህበረሰብ አገልግሎት፣ ከዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር እና የሴቶችን ተሳትፎ ከማሳደግ አንጻር የተከናወኑ አበይት ተግባራትን እና ይህን መነሻ በማድረግ በ2018 ዓ.ም ለመፈጸም በእቅድ ተይዘው ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የተፈራረሟቸው የKPI የትኩረት አቅጣጫዎችን የተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።
በቀረበው የKPI የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና እቅድ ላይ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱም በ2017 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም የታዩ ክፍተቶችን በመሙላት በ2018 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲውን በተሻለ አፈጻጸም ወደፊት ለማስኬድ ይጠቅማሉ የተባሉ ሃሳብ፣ አስተያየትና ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች የቀረቡ ሲሆን ውይይቱን ከመሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል።
በመጨረሻም ፕሬዚዳንቱ የተግባር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲን እውን ለማድረግ ሁሉም ኃላፊዎች ተቆጥረው የተሰጡንን የKPI ተግባራት በተዋረድ ላሉ የስራና ትምህርት ክፍሎ በማውረድና ግንዛቤን በመፍጠር KPIን መሰረት ባደረገ መልኩ መስራትና የተሰሩ ስራዎች በአግባቡ ተቆጥረው ሪፖርት መደረግ እንዳለባቸው በማሳሰብ የቀጣይ የስራ አቅጣጫን አስቀምጠዋል።