ወሎ ዩኒቨርሲቲ ሞደል ት/ቤት በኮምቦልቻ ከተማ ለመገንባት የቦታ ርክክብ አካሄደ
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ለሀገር የሚተርፉ ተማሪዎችን ለማውጣት የሚያስችል ሞደል ት/ቤት ለመገንባት ከኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ጋር የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም የቦታ ርክክብ አካሄደ።
ዩኒቨርሲቲው ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የሚሰጥ ሞደል ትምህርት ቤት ለማስጀመር የሚያስችል ስምምነት ነው ከከተማ አስተዳደሩ ጋር የተፈራረመው።
ስምምነቱን የተፈራረሙት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አወል ሰይድ እና የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሀመድ አሚን ናቸው።
ትምህርት ለማህበረሰብ እድገትና ለውጥ ቁልፍ መሣሪያ እንደመሆኑ መጠን ለኮምቦልቻ ከተማ እና ለአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጥ ሞዴል ትምህርት ቤት ባለመኖሩ የዚህ ስምምነት ፋይዳው ትልቅ እንደሆነ ተገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው በማህበረሰብ አገልግሎት በኩል ጥናትና ምርምር በማድረግ ይበልጥ ወደ ህብረተሰቡ ዘልቆ በመግባት ዘርፈ-ብዙ ተግባራትን እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።
ወሎ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት