ወሎ ዩኒቨርሲቲ በአንበጣ የተጎዱ የአገዳ ሰብሎች ለእንሰሳት መኖ እንድቀናበሩ አደረገ። ====
  November 11, 2020    News

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በአንበጣ የተጎዱ የአገዳ ሰብሎች ለእንሰሳት መኖ እንድቀናበሩ አደረገ። ================== በምስራቅ አማራ ከፍተኛ የአንበጣ መንጋ ጉዳት በደረሰባቸው የወረባቦና ባቲ ወረዳ ያሉ የአገዳ ሰብሎችን ለእንሰሳት መኖ በማቀናበር የቴክኖሎጂ ሽግግር ተካሄዷል። ከአንበጣ ጉዳት የተረፉ የአገዳ ሰብሎችን በተለያዩ የመኖ ግብዓቶች በማበልጸግ ለእንሰሳት ምግብ እንደት መጠቀም እንደሚቻል ለአርሶ አደሩ ቴክኖሎጂውን ለማስፋፋት ተችሏል። የወሎ ዩኒቨርሲቲ የስኳር ፋብሪካ ተረፈ ምርቶችን (molasses) ከማሽላ አገዳ ጋር በማቀላቀል የበለጸገ የእንሰሳት መኖ በባቲና ወረባቦ ወረዳዎች በማዘጋጀት ቴክኖሎጂው ወደ አርሶ አደሩ እንድሸጋገር አድርጓል። ዩኒቨርሲቲ የመኖ ግብዓቶችንና የማዘጋጃ ጆመብሬይን ግዥ በመፈጸም በእንሰሳት ህክምና ሳይንስ ት/ቤት :የግብርናና ተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ ባለሙያዎች በሳይንሳዊ መንገድ የእንሰሳት መኖ እየተቀናበረ ቴክኖሎጂውን ለማሸጋገር ችሏል።