በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በመከላከል የመማር ማስተማር ስራውን ለማስቀጠል ከመምህራን ጋር ምክክር ተደረገ
  October 15, 2020    News

በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በመከላከል የመማር ማስተማር ስራውን ለማስቀጠል ከመምህራን ጋር ምክክር ተደረገ፡፡ በዚህ አላማውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በመከላከል የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል ታሳቢ ባደረገው የግንዛቤ መድረክ ላይ የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በወሎ ዩኒቨርሰቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ በበኩላቸው ስለስልጠናው ፋይዳ ግንዛቤ ፈጥረዋል፡፡ መድረኩ በሶስት አበይት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን ኮሮና ቫይረስ ከህግ አግባብ ያለው ትርጓሜ፣ አስከትሎቱና ቅጣቱ ከህግ ትምህርት ክፍል በመጡ ምሁራን በሰፊው የተዳሰሰ ሲሆን ከጤና ችግርነቱ አኳያ ደግሞ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን ገለጻ አቅርበዋል ከዚሁ ጎን ለጎን የስነ ባህሪ ትምህርት ክፍል በበኩሉ ተማሪዎች በሚኖራቸው ቆይታ ሊፈጠር የሚችልን የስነ ልቦና ችግር ምክንያት በማድረግ መምህራንና የተቋሙ ሰራተኞች በማማከር እና ድጋፍ በመስጠት የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ሊወጡ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡ መድረኩ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በመቆጣጠር የመማር ማስተማር ስራውን ለማሳለጥ ትኩረት ከማድገጉ ባሻገር ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን ለመፍጠር ምን እናድርግ በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል፡፡