ወሎ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ወረርሽኝ እየተከላከለ የስልጠና ፕሮግራሙን ለማስቀጠል ውይይት አካሄደ።
  October 10, 2020    News

ሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኔስተር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያለውን የስልጠና ፕሮግራም ለማስቀጠል የኮሮና ወረርሽኝ አስመልክቶ በተዘጋጀ የተቋማት መተዳደሪያ መመሪያ ላይ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ውይይት ተካሄዷል። ይህ የመተዳደሪያ መመሪያ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰሩ መምህራና ሰራተኞች የኮሮና ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል ከጤና አኳያ መተግበር ባለባቸው ተግባራቶችና መመሪያውን በማይፈጽሙ ሰራተኞች ላይ ከህግ አግባብ በሚወሰዱ ርምጃዎች ላይ ያተኮረ ነው። በዚህ ውይይት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አባተ ጌታሁን በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠውን ስልጠና ለማስቀጠል የተቋሙ ሰራተኞች ወረርሽኙን ለመከላከል የወጣውን የመተዳደሪያ ደንብ ከመፈጸም ባሻገር መምህራን የኮሮና ሴሚስተር ስልጠናን በ45 ቀን ለማጠናቀቅ በተመረጡ የስልጠና ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል። አያይዘውም ፕሬዚዳንቱ ሰልጣኝ ተማሪዎች የኮሮና ሴሚስተርን በ45 ቀን እንድሁም በ2013 ዓ ም የሚሰጠውን ሁለት ወሰነ ትምህርት ስልጠና በ120 ቀን ለማጠናቀቅ በሚሰራ ስራ ተማሪዎች እንዳይጨናነቁ በስነ ልቦና የማነጽና የማረጋጋት ስራ መምህራን መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል። ከኮሮና ወረርሽኝ ባሻገር ልዩ የፖለቲካ፣ የብሄርና የሀይማኖት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው በሚመጡ አካላት የተቋሙ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዳስተጓጎል ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ጭምር ተካሄዷል። በአጠቃላይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቋረጠው ስልጠና እንድቀጥል በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኔስተር የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን ወሎ ዩኒቨርሲቲ ቀድሞ በማሟላት ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን ሙሉ በሙሉ አጠናቋል።