በወሎ ዩኒቨርሲቲ የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለሰራተኞቹ የቅድመ ግንዛቤ ስልጠና ሰጠ
  October 07, 2020    News

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለሰራተኞቹ የቅድመ ግንዛቤ ስልጠና ሰጠ፡፡ —----------------------------- የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ጽ/ቤት በአገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በተማሪዎች ክሊኒክ ባለሙያዎች በስሩ ለሚገኙ ሰራተኞች የግንዛቤ ፈጠራ ሰልጠና ሲሰጥ መቆዬቱ የሚታወስ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ዳይሬክተር ጽ/ቤቱ በ2013 ዓ.ም የበጀት አመት የተማሪዎች አቀባበልንና መስተንግዶን በተመለከተ ምን መምሰል እንዳለበት የቅድመ ግንዛቤ ፈጠራ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ በያዝነው አመት በመጀመሪያው ዙር በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ4ኛ እና 5ኛ አመት አንድ ሺህ ሰባት መቶ ተመራቂ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለማጠናቀቅ አርባ አምስት ቀናትን የሚቆዩ ሲሆን በቆያታቸው ከእነሱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ባለሙያዎችና ተማሪዎች ለኮሮና ቫይረስ እንዳይጋለጡ በተማሪዎች ክሊኒክና የመማክርት አገልግሎት አጭር ስልጠናና የስራ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡