ወሎ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ሳይንስ ያሰለጠናቸውን 32 ሀኪሞች አስመረቀ
  October 07, 2020    News

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ሳይንስ ያሰለጠናቸውን 32 ሀኪሞች አስመረቀ። =================== ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከ2004 ዓ ም ጀምሮ በመጀመሪያ ድግሪ ተመርቀው በትምህርት ሚኔስተር የተሰጠ የህክምና ሳይንስ መግቢያ ፈተና ያለፉ ተማሪዎችን ተቀብሎ በህክምና ማሰልጠን ጀምሯል። ዩኒቨርሲቲው በሀገሪቱ ያለውን የሃኪም እጥረት በመቅረፍ የራሱን አስተዋዕኦ ለማበርከት ለ5 ዓመት ተኩል ያሰለጠናቸውን የህክምና ሳይንስ 25 ወንድና 7 ሴት በድምሩ 32 የህክምና ሳይንስ ሀኪሞች (ዶክተሮች) ተመርቀዋል። በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ከታካሚ ብዛትና ፍላጎት ጋር የሚጣጣም የህክምና አገልግሎት ተደራሽ እንድሆን የሰለጠኑ ሀኪሞችን ማፍራት ሀገራዊ ግደታ ጭምር ነው በማለት ንግግር ያደረጉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አባተ ጌታሁን (ዶ/ር) ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከ2009 ዓ ም ጀምሮ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ በህክምና ሳይንስ ያሰለጠናቸውን ሀኪሞች ለ4ኛ ጊዜ ማስመረቅ መቻሉን ገልጸዋል። በተጨማሪ ፕሬዚዳንቱ ታካሚዎች ባሏቸው የቋንቋ፣ የብሄር፣ የሀይማኖትና የጾታ ልዩነት ምክንያት የህክምና አድሎ ሳይኖር ተመራቂ ሀኪሞች ሁሉንም የህክምና የሙያ ስነ ምግባር በሚያዘው መሰረት ተገቢውን ሰብዓዊ አገልግሎት እንድሰጡ አሳስበዋል። ወሎ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን እየተከላከለ ጎን ለጎን የመማር ማስተማር ፕሮግራሙን በማስቀጠል በ2012 ዓ ም በድህረ ምረቃ ፕሮግራም ከ400 በላይ ተማሪዎችን ማስመረቁ ይታወቃል።