በጽናት የአካል ጉዳተኞች ማህበር ከወሎ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገለት። ===========================በጽናት የአካል ጉዳተኞች ማህበር ከወሎ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገለት። ===========================
  August 13, 2020    News

በ24 አባላት የተመሰረተው በጽናት የአካል ጉዳተኞች የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር በደሴ ከተማ ለሚያካሄደው የመስሪያ ቦታ ግንባታ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ ተደርጎለታል። ማህበሩ ነሀሴ 5/2012 ዓ ም ከወሎ ዩኒቨርሲቲ 300 ኩንታል ሲምንቶ፣ 300 የቤት ቆርቆሮና 17 ፓኮ የቆርቆሮ ሚስማር ተረክቧል።