ወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል ለአካባቢው ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የፊት መሸፈኛ ማስክ ሰርቶ አስረከበ፡፡
  June 26, 2020    News

የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ቴክስታይል፣ ሌዘር እና ጋርመንት ት/ቤት መምህራን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በሚል አስካሁን ያመረታቸውን አስር ሺህ ያህል የፊት መሸፈኛ ማስኮች ለተለያዩ የህብረተሰብ አካላት እንዲሰራጭ አድርጓል፡፡ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ በተለያዬ ጊዜያት ለሚመለከታቸው አካላት የፊት መሸፈኛ ማስኮችን ሰርቶ ያስረከበ ሲሆን ባጠቃላይ ያመረታቸውን አስር ሺህ የፊት መሸፈኛ ጭምብሎች ለወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች፣ ለደሴ ከተማ አስተዳደር፣ ለባቲ ኳረንታይን ሴንተር፣ ለደቡብ ወሎ ዞን፣ ለኦሮሚያ ልዩ ዞን፣ ለኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር፣ ለደሴ ውሃ ስራዎች፣ ለግብርና ምርምር ተቋም፣ ለሳይንትና ደላንታ ወረዳዎች ሌሎች አካላት አከፋፍሏል፡፡ የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቴፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር መላኩ ታመነ በግቢው የሚመረቱት ሶስት ሽፋን ያላቸው ማስኮች በጥራትና ምቾት ተመራጭ መሆናቸው በብዛት እንደሚመረቱ እንዳስቻለ ገልጸው በስራው ለተሳተፉ የቴክስታይል ት/ቤት መምህራንና ሂደቱን ሲያስተባብር ለነበረው የት/ቤቱ ዲን አቶ ቴዎድሮስ አጋዥ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡