ወሎ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የበጎ ፍቃደኞች ስልጠና ሰጠ። ===========================
  May 11, 2020    News

በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የወሎ ዩኒቨርሲቲ በደሴ ከተማ በበጎ አድርጎት ለተሰማሩ ወጣቶች ስልጠና ሰጥቷል። ስልጠናው የተዘጋጀው በበጎ ፈቃደኝነት የተሰማሩ ወጣቶች ራሳቸውን ከቫይረሱ ተከላክለው ማህበረሰቡን በምን መልኩ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ግንዛቤ ለመፍጠር ነው። ለሰልጣኞች መልእክት ያስተላለፉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አባተ ጌታሁን በምስራቅ አማራ ቫይረሱን ለመከላከል ዩኒቨርሲቲው፣ ደሴ ከተማና ደቡብ ወሎ በጋራ በመሆን 5 (አምስት) የህክምና ማእከላትን እና ግብአቶችን በማሟላት ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል። እነዚህ የህክምና ማእከላትን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ለማህበረሰቡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡ ወጣቶችን በማሰልጠን ወደ ስራ ለማስገባት ስልጠናው የተዘጋጀ እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል። ስልጠናው 200 ለሚሆኑ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ለሆኑ ወጣቶች ተሰጥቷል። Wollo University has given a training for good permits to protect corina virus. =========================== In a short time, Wollo University has given training to the youth who are being burned in Dessie City. The Youth who are prepared for the power is to create awareness of how they should provide service to the community. The President of Wollo University President Dr. Abate Getahun has announced that he has been prepared to protect his virus in East Amhara, DESSIE CITY AND SOUTH WOLLO 5 (five) Medical Center and Egypt. The President has announced that the president has been prepared to work for the community, including the medical center, including these medical center. The phone has been given to youth who are willing to provide good permission for 200