ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከኢንዶንዥያ ኤንባሲ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት መሰረተ።
  November 14, 2019    News

የኢንዶንዥያ ኤንባሲ ልኡክ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሄዷል። በውይይቱ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ መምህራን፣ ሰራተኞችና ተማሪዎች ተገኝተዋል። በዚህ የሁለትዮሽ ውይይት ንግግር ያደረጉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አባተ ጌታሁን በወሎ ህዝብ እና በኢንዶንዥያ ህዝብ መካከል ተቀራራቢ የሆኑ ባህላዊ፣ ሀይማኖታዊና አርኪኦሎጅካዊ መስተ-ጋብሮችን በማሳደግ በሰላምና በትምህርት ላይ በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል። አያይዘውም ፕሬዚዳንቱ ኢንዶንዥያ 700 ዩኒቨርሲቲዎችና ከ300 በላይ ደግም የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ካሏት ሀገር ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት መመስረቱ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የተሻለ የትምህርት እድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል። የኢንዶንዥያ ኤንባሲ ፐፕሊክ ዲፕሎማሲ ልኡክ ተወካይ በበኩላቸው በኢንዶንዥያና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት በማንሳት ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል። ልኡኩን በመወከል ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የኤንዶንዥያ አምባሳደር Mr Albushira Basnur የኢንዶንዥያ ኤንባሲ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ትኩረት ሰጥቶ ባነሷቸው በባህል፣ በሰላም፣ በሰው ሀብት ልማት/ scholar/ እንድሁም ዩኒቨርሲቲው በሚፈልጋቸው ተያያዥ መስኮች በትብብር ለመስራት ፍቃደኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ኤንባሲውም በኤንዶንዥያ በሚገኙ የከፍተኛ ት/ተቋማት ለወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ሰራተኞችና ተማሪዎች የስኮላር የትምህርት እንድል የመስጠት ፍላጎት እንዳለው አመላክቷል።