በወሎ ዩኒቨርሲቲ የESTEM የቤተ ሙከራ ማእከል ተከፈተ።
  November 14, 2019    News

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጅ፣ በኢንጅነሪንግና በሒሳብ የትምህርት መስኮች የተሻለ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች እንድኖሩ የESTEM ማእከል በማቋቋም እየሰራ ይገኛል። ይህንን የESTEM ማእከል በቴክኖሎጅ ለማደራጀት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር " የኮምፒዩተርና የኤሊክትሮኒክስ" ቤተ-ሙከራ ከፍቷል። ይህ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የESTEM power ማበልጸጊያ "የኮምፒተርና የኤሌክትሮኒክስ ቤተ ሙከራ" በአሜሪካን ESTEM power.org ከተሰኘ ድርጅት በተገኘ ድጋፍ የተመሰረተ ነው። ማእከሉ በዘመናዊና ደረጃቸውን በጠበቁ የቤተ-ሙከራ ማቴሪያሎች የተደራጀ እንድሆን ድርጅቱ ሁሉንም መሳሪያዎች በቀጥታ ከውጭ እንድገቡ አድርጓል። ይህም የESTEM ማእከል የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራንና ድጋፍ አድራጊው የESTEM power ድርጅት ተወካይ ባሉበት "ማእከሉ" በይፋ ተከፍቷል።