ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለአፋር ክልል ተወላጆች የትምህርት እድል ሰጠ።
  October 09, 2019    News

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በደቡብ ወሎ፣ በደሴ ከተማና በከሚሴ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር የላቀ አፈጻጸም በየዓመቱ ለሚያስመዘግቡ የመንግስት ሰራተኞች የትምህርት እድል ይሰጣል። ዩኒቨርሲቲው በ2012 ዓ ም ተደራሺነቱን ወደ አፋር ክልል በማስፋት ለ100 የመንግስት ሰራተኞች ነጻ የትምህርት እድል ሰጥቷል። የትምህርት እድሉም በቅድመ ምረቃ ለ25ቱ በመደበኛ ለ25ቱ በኤክስቴንሽን፥ በድህረ ምረቃ ፕሮግራም ደግሞ ለ25ቱ በመደበኛ ለ25ቱ በኤክስቴንሽን እንድሰለጥኑ የተሰጠ ነው። ከአካባቢው ማህበረሰብ ባለፈ ዩኒቨርሲቲው ነጻ የትምህርት እድል ለአፋር ክልል መስጠቱ በተቋሙና በክልሉ መካከል ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር በቀጣይ ክልሉ የዩኒቨርሲቲው አንዱ የምርምር መዳረሻ ሊሆን ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። ወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2011/12 ዓ ም በክረምት በማጠናከሪያነት በሚሰጠው የESTEM ፕሮግራም ከ9ኛ ወደ 10ኛ ክፍል አንደኛ በመውጣት ለተዛወሩ 40 የአፋር ክልል ተማሪዎች እድል ሰጥቶ 23ቱ በዩኒቨርሲቲው ቆይተው መመለሳቸው ይታወቃል።