ወሎ ዩኒቨርስቲ የማኅበረሰብ ተኮር ሬዲዮ ጣቢያ በማቋቋም ሕብረተሰቡን ለማገልገል እየሠራ መሆኑን ገለጸ። Call for papers:
  June 20, 2022    News

ወሎ ዩኒቨርስቲ የማኅበረሰብ ተኮር ሬዲዮ ጣቢያ በማቋቋም ሕብረተሰቡን ለማገልገል እየሠራ መሆኑን ገለጸ። ደሴ: ሰኔ 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ወሎ ዩኒቨርስቲ የማኅበረሰብ ተኮር ሬዲዮ ጣቢያ ምስረታ ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል። የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር መንገሻ አየነ የማኅበረሰብ ተኮር ሬዲዮ ጣቢያ መገንባቱ የሚኖረው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ዩኒቨርስቲው የሬዲዮ ጣቢያውን ስርጭት ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን ገልጸዋል። በዩኒቨርስቲው የምርምር እና የማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ኀይሉ የማኅበረሰብ ተኮር ሬዲዮ ጣቢያው እንዲቋቋም አስተዋፆኦ ያበረከቱ አካላትን አመስግነዋል። ዩኒቨርስቲው በወራሪው ቡድን ከፍተኛ ዘረፋ እና ውድመት ቢፈፀምበትም ከመማር ማስተማር በተጨማሪ የተለያዩ የማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል። ዘጋቢ:–አንዋር አባቢ ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼ ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼ ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq በዌብሳይት amharaweb.com በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ ትዊተር https://bit.ly/336LQaS ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/