ወሎ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ መጻሕፍትን በእርዳታ አገኘ። =========================
  June 20, 2022    News

ወሎ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ መጻሕፍትን በእርዳታ አገኘ። ========================= ሰኔ 13 ቀን 2014 ዓ.ም (ወዩ ህ/ግንኙነት) የጠበቃ በለጠ አለሙ ፈለቀ ባለቤት ወ/ሮ ተናኘወርቅ ኃይሌ እና ልጆቻቸው ወ/ሮ ቅድስት አያሌው እና ምግባር አያሌው በአካል ዩኒቨርሲቲያችን ድረስ በመምጣት ከ525 በላይ የሆኑ የህግ፣ የታሪክ፣ የሃይማኖትና የስነጽሁፍ መጻህፍትን አስረክበዋል። አቶ በለጠ አለሙ ዛሬ በህይወት ባይኖሩም ከ18 አመታቸው ጀምሮ 86 አመት እስኪሆናቸው ድረስ በተለያየ ጊዜ እየገዙ ያጠራቀሟቸውን ቤተመጻህፍታቸው ውስጥ የነበሩትን ልዩ ልዩ ሙያዊ መጻህፍት ባለቤታቸውና ልጆቻቸው ለዩኒቨርሲቲያችን በታላቅ ደስታ አስረክበዋል። የጠበቃ በለጠ አለሙ ልጆች እንደገለጹልን አባታቸው በ80 አመታቸው በከፍተኛ ውጤት የህግ ዲግሪያቸውን እንደተቀበሉ ገልጸው አባታቸው የተማሩባቸውንና ለስራቸው የተገለገሉባቸውን መጻህፍት ለወሎ ዩኒቨርሲቲ በማበርከት ተማሪዎች እንዲገለገሉባቸው በማሰብ እንዳመጧቸው ነግረውናል። መጻህፍቱን የተረከቡት የቤተመጻህፍቱ ዳይሬክተር አቶ ሙሉነህ እንዳለ በበኩላቸው የተረከቧቸው መጻህፍት በገበያ ላይ ለማግኘት አስቸጋሪ የሆኑ የቆዩ ፣ ነገር ግን እጅግ ጠቃሚ ከመሆናቸውም በላይ በተለይ ለህግ፣ ለስነጽሁፍ እና ለታሪክ ተማሪዎች ጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁመው ለጋሾችን አመስግነዋል።