የተንታ አትሌቲክስ ማዕከል በ2014 ዓ ም የውድድር ዘመን 49 መዳሊያዎችን በመሰብሰብ አመርቂ ውጤት አስመዘገበ።
  June 20, 2022    News

የተንታ አትሌቲክስ ማዕከል በ2014 ዓ ም የውድድር ዘመን 49 መዳሊያዎችን በመሰብሰብ አመርቂ ውጤት አስመዘገበ። ======== የተንታ አትሌቲክስ ማዕከል በ2014 ዓ ም በሀገር አቀፍና በአማራ ክልል የአትሌቲክስ ክለባትና ማዕከላት ሻምፒዮና ውድድር ላይ በመሳተፍ 13 ወርቅ፣ 14 ብር፣22 ነሀስ በድምሩ 49 መዳሊያዎችን በመሰብሰብ የላቀ ውጤት አስመዝግቧል። አትሌቲክስ ማዕከሉ በሀገር አቀፍ ውድድሩ በ3000 ሜትር አንድት አትሌት በማስመረጥ በ2022 አለም አቀፍ ውድድር ላይ በማሳተፍ የድፕሎማ ተሸላሚ ሁኗል። የወሎ ዩኒቨርሲቲ አትሌቲክስ ማዕከሉ እያስመዘገበ ያለውን ውጤት በማየት በቀጣይ ማዕከሉ በሀገርና አለም አቀፍ ውድድሮች ደምቀው እንድታዩ ለአሸናፊ አትሌቶች የሽልማት ፕሮግራም አካሄዷል፡ በዚህ የሽልማት ፕሮግራም ላይ የተገኙት የወሎ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገ/ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር አማረ ምትኩ አትሌቲክስ ማዕከሉ ባስመዘገበው ውጤት የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ እየተቀዛቀዘ የመጣውን የተተኪ አትሌት የማፍራት እንቅስቃሴ ለመቅረፍ ወሎ ዩኒቨርሲቲ የጀመረውን ተግባር እንደሚያስቀጥል ገልጸዋል። የወሎ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት አካዳሚ ፕሬዚዳንትና የተንታ አትሌቲክስ ማዕከል የቦርድ አባልና የቴክኒክ አማካሪ ረ/ፕሮፌሰር ተገኝ ተሰማ ውጤታማ አትሌቶችን ለማነቃቃት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ለወርቅ፣ ለብርና ነሀስ መዳሊያዎች የ1200፣ 800 እና 600 ብር ሽልማት በቅደም ተከተል እንደሰጠ ገልጸዋል። አያይዘውም ረ/ፕሮፌሰሩ እንደገለጹት በቸክ ሪፕብሊክና በመሮኮ ራባት ላይ በዳይመንድ ሊክ ውድድር በ3000 ሜትር በመሳተፍ 6ኛ በመውጣት የድፕሎማ ተሸላሚ ለሆነችው አትሌት ጽዮን አበበ የ10 ግራም የአንገት ሀብት ሽልማት ተበርክቶላታል። በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው በተያዘው የውድድር ዘመን ለአትሌቶች ውጤታማነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ቡድን መሪ፣ አሰልጣኝ፣ ወገሻ እና ሌሎች አካላት የማበረታቻ ሽልማቶችን ሰጥቷል።