ባህርዳር ከተማ በመሳተፍ ላይ ያለው የወሎ ዩኒቨርሲቲ የተንታ አትሌቲክስ ቡድን አንጸባራቂ ድል አስመዘገበ።
  June 09, 2022    News

ባህርዳር ከተማ በመሳተፍ ላይ ያለው የወሎ ዩኒቨርሲቲ የተንታ አትሌቲክስ ቡድን አንጸባራቂ ድል አስመዘገበ። ========++=========+++++++====== ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም (ወዩ ህ/ግ) ባህርዳር ከተማ ላይ እየተካሄደ ባለው 2ኛው አገራቀፍ የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት ወድድር በወሎ ዩኒቨርሲቲ የተንታ አትሌቲክስ ማዕከል አትሌቶች ድል እያስመዘገቡ ነው። ዛሬ በማለዳው ከደቂቃዎች በፊት በተደረገው 10000 ሜትር የወንዶች የፍጻሜ ውድድር በወሎ ዩኒቨርሲቲ ከተንታ አትሌቲክስ ማዕከል የተገኙት አትሌት አቤል በቀለ 1ኛ፣ አትሌት ታሪኩ አንተነህ 2ኛ እና አትሌት መልካሙ ጋሻው 4ኛ በመሆን የበላይነቱን ይዘው አጠናቀዋል። ከዚህም በተጨማሪ በቃሉ አደመ በስሉስ ዝላይ 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያውን በእጁ አስገብቷል። እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ!!