የወሎ ዩኒቨርሲቲ ነባሩና አዲሱ የስራ አመራር ቦርድ አባላት የመስክ ጉብኝትና የስራ ርክክብ አደረጉ።
  June 09, 2022    News

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ነባሩና አዲሱ የስራ አመራር ቦርድ አባላት የመስክ ጉብኝትና የስራ ርክክብ አደረጉ። ========+++++++++=========== ረቡዕ ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ.ም (ወዩ ህ/ግ) የወሎ ዩኒቨርሲቲ አዲሱ የስራ አመራር ቦርድ በትምህርት ሚኒስቴር በተደረገ አዲስ ምደባ ከሚያዚያ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ሃላፊነቱ መሰጠቱ ይታወቃል። በመሆኑም ነባሩ የስራ አመራር ቦርድ አባላት የተሰጣቸውን ኃላነቶችንና ስራዎችን ለአዲሱ የስራ አመራር ቦርድ አባላት በይፋ በዛሬው እለት ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ.ም አስረክበዋል። ኃላፊነታቸውን ላስረከቡ የአመራር ቦርድ አባላት እውቅና እና ስንብት የተደረገ ሲሆን ለአዳዲስ የቦርድ አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በርክክቡ ወቅት የቦርድ ሰብሳቢው ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ እና የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ተገኝተዋል። ነባሩ እና አዲሱ የስራ አመራር ቦርድ አባላት እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትና ም/ፕሬዝዳንቶች በተገኙበት በ2015 ዓ. ም ስራ የሚጀምረውን የጢጣ ግቢ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። ከጉብኝቱ በኋላ በተደረገ የጋራ ውይይት ዩኒቨርሲቲውን ለማሳደግ ከመቸውም ጊዜ በተሻለ በትብብርና በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ታመኗል።