የጅማ ዩኒቨርሲቲ የምግብ አቅራቢ ድርጅቶች ለወሎ ዩኒቨርሲቲ የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።
  April 10, 2022    News

የጅማ ዩኒቨርሲቲ የምግብ አቅራቢ ድርጅቶች ለወሎ ዩኒቨርሲቲ የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ። ================ የወሎ ዩኒቨርሲቲ መልሶ ለማቋቋም 13 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እያስተባበረ ያለው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲውን መልሶ ለማቋቋም ለተለያዩ ድርጅቶች ጥሪ አድርጓል። የጅማ ዩኒቨርሲቲን የድጋፍ ጥሪ ተከትሎ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ የተለያዩ ድርጅቶች አወንታዊ ምላሽ መስጠት ጀምረዋል። የመጀመሪያ ምላሽ የሰጠው የጅማ ዩኒቨርሲቲ የምግብ አቅራቢ ድርጅት 55 ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ ለወሎ ዩኒቨርሲቲ አድርጓል። ድጋፍን ለወሎ ዪኒቨርሲቲ ያስረከቡት የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ በዩኒቨርሲቲ ለሚሰሩ ተቋራጮችና ድርጅቶች ባደረግነው ጥሪ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምግብ አቅራቢ ድርጅት ድጋፉን ሰጥቷል ብለዋል። እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ ከሆነ ሌሎችም ድርጅቶችንና ተቋራጮች ተመሳሳይ ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።