ወሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመስራት ከኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጅ ኢንስቶዩት ጋር ተፈራረመ።
  April 06, 2022    News

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመስራት ከኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጅ ኢንስቶዩት ጋር ተፈራረመ። ================ ወሎ ዩኒቨርሲቲ በምርምር፣ በመማር ማስተማር፣ በሙያ ድጋፍ፣ በስልጠናና በሌሎች ዘርፎች ከኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል። የኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት በጦርነት የተጎዳውን ወሎ ዩኒቨርሲቲ እና በዩኒቨርሲቲው ጎን ያለውን ቲሹ ካልቸር በምርምር ዘርፍ ገንዘብ ከመደገፍ ጀምሮ የሁለተኛና ሶስተኛ ድግሪ ተማሪዎችን በመደገፍ በጋራ ለመስራት መስማማቱን ገልጿል። ወሎ ዩኒቨርሲቲ በbio-science and emergency technology የጀመረውን የልህቀት ማዕከል እውን ለማድረግ ከኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር ለመስራት መስማማቱ ዘርፉን ለማሳደግ እንደሚያስችለው ተገልጿል።