ወሎ ዩኒቨርሲቲ በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች የምግብ ድጋፍ አደረገ። ===============
  October 13, 2021    News

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች የምግብ ድጋፍ አደረገ። =============== ህወሀት መራሹ የጥፋት ቡድን በአፋር ክልል በፈጸመው ወረራ ለተፈናቀሉ ዜጎች የወሎ ዩኒቨርሲቲ 100 ኩንታል የስንዴ ዱቄትና 93 ኩንታል ሩዝ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉን ያስረከቡት የወሎ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌትነት ካሴ የወሎና የአፋር ህዝብ አንድ አይነት ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ትስስር ያለው አንድ ህዝብ ሲሆን የአፋር ህዝብ ችግር የወሎም ህዝብ ችግር በመሆኑ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ከጎናቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የምግብ ድጋፍ አድርጓል ሲሉ ገልጸዋል። ድጋፉን የተረከቡት የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የሀብትና ንብረት ዳይሬክተር ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለአፋር ተፈናቃዮች ያደረገው ድጋፍ ለአፋር ህዝብ ያለውን ተቆርቋሪነትና አንድነት ያሳየ መልካም ተግባር ነው ሲሉ ተናግረዋል። ወሎ ዩኒቨርሲቲ ድጋፉ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ በኩል ለተፈናቃዮች ተደራሽ እንድሆን ድጋፉን ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ አስርክቧል።