የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአስር አመት ስትራቴጂክ እቅድ ለመስራትና የመዋቅር ለውጥ ለማካሄድ ውይይት አካሄደ። =================
  October 13, 2021    News

የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአስር አመት ስትራቴጂክ እቅድ ለመስራትና የመዋቅር ለውጥ ለማካሄድ ውይይት አካሄደ። ================= የወሎ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በኮሌጁ ሊደርስበት የሚቻል ሁለተናዊ ለውጥ የሚያመጣ የአስር አመት ስትራቴጂክ እቅድ እና ሊያሰራ የሚያስችል መዋቅር ለመዘርጋት እየሰራ ነው። ኮሌጁ የአስር አመት ስትራቴጂክ እቅድ ለመቅርጽና ሊያሰራ የሚያስችል መዋቅር ለመቅረጽ ውይይት አካሄዷል። በዩኒቨርሲቲው ካሉ ኮሌጆች በፕሮግራም ፣ በሰው ሀይል እና በተማሪ ብዛት የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ላቅ ያለ ድርሻ ይዞ ይገኛል ያሉት የኮሌጁ ም/ዲን ዶ/ር ታደሰ ሲሳይ ኮሌጁ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጭምር የተሰጠውን የልህቀት ማዕከልነት ከግብ ለማድረስ ሳይንሳዊ መሰረት ያለው የአስር አመት ስትራቴጂክ እቅድና መዋቅራዊ አደረጃጀት ማካሄድ ይጠበቅበታል ብለዋል። አያይዘውም ም/ዲኑ ኮሌጁ ተወዳዳሪ የጤና ባለሙያዎችን ለማፍራት የሚያስችል መሪ እቅድ እና መዋቅራዊ አደረጃጀት እንድኖረው ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተሞክሮዎችን በመቀመር በኮሌጁ ካሉ የት/ክፍል ሀላፊዎችና አስተባባሪዎች ጋር ውይይት ተካሄዷል ሲሉ ገልጸዋል። በውይይቱ የተሳተፉ የትምህርት ክፍል ሀላፊዎችና ኮሚቴዎች የኮሌጁን የተሻለ የአስር አመት መሪ እቅድ ለማቀድና የተሻለ መዋቅራዊ አደረጃጀት ለመፍጠር ከውይይቱ በቂ ግብዓቶችን እንዳገኙ ገልጸዋል።