ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በሰሜን ወሎና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖች የአልባሳትና የምግብ ድጋፍ አደረገ፡፡ =====================================================
  October 13, 2021    News

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በሰሜን ወሎና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖች የአልባሳትና የምግብ ድጋፍ አደረገ፡፡ ===================================================== የወሎ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ላሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያደረገውን የድጋፍ ጥሪ ተከትሎ በጎ ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ይህንኑ ጥሪ መሰረት በማድግ በርካታ የተለያዩ ከፍተኛ ትምህረት ተቋማት ተወካዮች ተፈናቃዮች ያሉበትን ሁኔታ በማየት በርካታ ድጋፎችን አድርገዋል፤ በማድረግም ላይ ይገኛሉ፡፡ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲም 1.139.000 (አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሽህ ብር) የሚያወጣ የተለያዩ የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል፡፡ ድጋፉን አስመልክቶ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲዎች ካላቸው ላይ በማካፈል፤ ለወገኖች መድረስ ትርጉሙ ትልቅ ነው ካሉ በኋላ ዩኒቨርሲቲያችን ያደረገው ድጋፍ ካለው የተፈናቃይ ቁጥርና ጉዳት አንጻር በቂ ባይሆንም ለወገኖቻችን አለንላችሁ ለማለትና ድጋፋችንን ለማሳየት መጥተናል ብለዋል፡፡ ድጋፉም ተፈናቀይ ወገኖቻችን ወደ መኖሪያቸው ሲመለሱ ማቋቋም ስለሚያስፈልግ ሁሉም መተባበር እንዳለበትና በዩኒቨርሲቲያቸው በኩልም እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች የአንድነት ማሳያ፣ የዕውቀት መፍለቂያ፣ የችግር መፍቻ ቁልፍ እንደመሆናቸው እነዚህንና መሰል ችግሮች እንዳይከሰቱ ከተከሰቱም በቀላሉ የሚፈቱበትን በጥናትና ምርምር የተደገፈ መፍትሄ ማስቀመጥ ያሻል፡፡ ስለሆነም እንዲህ ዓይነቱ ድጋፍ የህዝብ ለህዝብ ትስስርንና አንድነትን ይፈጥራል ብለዋል፡፡