አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ 1.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ምግብ እና ቁሳቁስ ደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ
  September 08, 2021    News

አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ 1.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ምግብ እና ቁሳቁስ ደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ ===========//========== ከሰሜን ወሎ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደሴ ከተማ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮችን ለመደገፍ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ባቀረበው ጥሪ መሰረት አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ 1.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት የምግብ እና ቁሳቁስ እርዳታ ለግሷል። የመጣውን ድጋፍ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገዝሙ ቀልቦ ለወሎ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ እና ለማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተት ዶ/ር ጌታቸው ጉግሳ አስረክበዋል። በተደረገው ጥሪ መሰረት ከተለያዩ ዩነቨርሲቲዎች እየመጣ ያለው ድጋፍ በከተማ አስተዳደሩ በኩል ለተፈናቃዮች እየተከፋፈለ መሆኑንም ዶ/ር ጌታቸው ጉግሳ ገልፀዋል። በዚሁ አጋጣሚ ለሚደረገው ድጋፍ ሁሉ እያመሰገንን ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች በርካታ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ወደ ነበሩበት እስኪመለሱ ድረስ ቀጣይነት ያለው ድጋፋችሁን እንድታደርጉ ለሚመለከታችሁ ሁሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።