በአማራ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፎረማቸው ለተፈናቃዮች ድጋፍ ለማድረግ ወሰኑ። ================
  September 08, 2021    News

በአማራ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፎረማቸው ለተፈናቃዮች ድጋፍ ለማድረግ ወሰኑ። ================ የህወሀት ጽንፈኛ ሀይል በአማራ ህዝብ ላይ ባካሄደው ወረራ ከሀብት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳት በአማራ ክልል የሚገኙ 10ሩ ዩኒቨርሲቲዎች በወሎ፣ በንፋስ መውጫና በደባርቅ ግንባሮች በጉድኝት እየሰሩ ነው። በወሎ ግንባር የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳት የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ድጋፉን ይዞ ቀድሞ ደሴ የገባ ሲሆን ደብረማርቆስ፣ እንጅባራና ደብረ ብረሃን ዩኒቨርሲቲዎች በቅርብ ቀን ለወገን ያላቸውን አጋርነት እንደሚያሳዩ ይጠበቃል። የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግምቱ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት 200 ኩንታል ነጭ ዱቄትና 500 ጥንድ አንሶላ በወሎ ዩኒቨርሲቲ በኩል ለተፈናቃዮች እንድደርስለት አስረክቧል።...