የላኮመልዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። ================
  September 08, 2021    News

የላኮመልዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። ================ ወሎ ዩንቨርስቲ የፌደራል የከፍተኛ ትምህርት ተቆማትን በማስተባበር ከ12 ሚሊዬን ብር በላይ የአይነት ድጋፍ ከሰሜን ወሎ፣ ከዋግምራና ወልዲያ ከተማ ለተፈናቀሉ ከመቶ ሃያ ሺህ በላይ ሰዎች ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ዩኒቨርሲቲው የድጋፍ አቅርቦቱ በማስቀጠል ከተቋሙ የላኮመንዛ ንግድና ማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ከሩብ ሚሊዬን ብር በላይ የሚገመት ቁሳቁሶችን በግዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ለሚገኙ ተረጅዎች በአካል በመገኘት አስረክበዋል። ከዚህ በተጨማሪም ኢንተርፕራይዙ በተለያዬ መልኩ ድጋፉ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢንተርፕራይዙ ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ ሰለሞን ተናግረዋል። ሃላፊው አያይዘውም እንደገለፁት ኢንተርፕራይዙ በገንዘብና በአይነት ከሚያከናውነው ድጋፋ በተጨማሪም በአገልግሎት ዘርፍ ዝነኛው የወሎ ባህል ቡድንን በመጠቀም ግንባር ላይ ለተሰለፉት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በግንባር በመገኘት ተከታታይ የወኔ ስንቅ እያቀረበ መሆኑ እንዲሁም ተፈናቃዬች በሚገኙባቸው ግዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች የተላላፊ በሽታዎች እንዳይከሰቱ የጤና ኮሌጅ እያደረገው ከሚገኘው ድጋፍ ጎን ለጎን የኢንተርፕራይዙ የፍሳሽ መኪኖች የማያቋርጥ የፅዳት አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አስገንዝበዋል።