የዋቻሞና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች ድጋፋቸውን ለወሎ ዩኒቨርሲቲ አስረከቡ ============= በወራሪው የህወሀት ጽንፈኛ ሀይል ምክንያት ቤት ንብረታቸውን ጥለው ወደ ደቡብ ወሎ ደሴና ኮምቦልቻ ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቻሉትን ድጋፍ በማድረግ ላይ ናቸው። የዋቻሞና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች ልዩ ልዩ ድጋፎችን በመያዝ በወሎ ዩኒቨርሲቲ በኩል ድጋፉ እንድደረግላቸው ይዘው የመጡትን ቁሳቁስ ለወሎ ዩኒቨርሲቲ አስረክበዋል። በዚህ የቁሳቁስ ድጋፍ የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን
  September 01, 2021    News

በወራሪው የህወሀት ጽንፈኛ ሀይል ምክንያት ቤት ንብረታቸውን ጥለው ወደ ደቡብ ወሎ ደሴና ኮምቦልቻ ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቻሉትን ድጋፍ በማድረግ ላይ ናቸው። የዋቻሞና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች ልዩ ልዩ ድጋፎችን በመያዝ በወሎ ዩኒቨርሲቲ በኩል ድጋፉ እንድደረግላቸው ይዘው የመጡትን ቁሳቁስ ለወሎ ዩኒቨርሲቲ አስረክበዋል። በዚህ የቁሳቁስ ድጋፍ የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በድምሩ ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል።