ወለጋና ጂንካ ዩኒቨርሲቲዎች የ4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።
  August 30, 2021    News

በኢትዮጵያ ያሉ የከፍተኛ ት/ተቋማት የወሎ ዩኒቨርሲቲን የድጋፍ ጥሪ ተከትሎ መልስ እየሰጡ ይገኛል። ይህንን ጥሪ ተከቶሎ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የ2 ሚሊዮን ብር የቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርግ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለወሎ ዩኒቨርሲቲ የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ለደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የ750 ሺ ብር በድምሩ ከ 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል። የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተፈናቃይ ዜጎች ያሉበትን ሁኔታ በአካል በማየት አይዟችሁ ከጎናችሁ ነን ለማለት በአካል ተገኝተው ድጋቻቸውን አድርገዋል።