9ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ።
  February 16, 2021    News

9ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ። ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከ2005 ዓ ም ጀምሮ በተከታታይ በየዓመቱ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው የተለያዩ የምርምር ጽንስ ሀሳቦችን ላይ ያተኮሩ ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ እያካሄደ ይገኛል። ዩኒቨርሲቲ በተያዘው የበጀት አመት 9ኛውን ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ በርካታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የምርምር ማዕከላት ተመራማሪዎችን ባሳተፈ መልኩ " the role of research and community engagement for economic growth and development" በሚል መነሻ ሀሳብ አካሄዷል። የምርምር አቅራቢዎችንና ተሳታፊዎችን እንኳን ወደ "የባህል እሴት አውድማ " ወሎ በሰላም መጣችሁ ያሉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተወካይ ዶ/ር መንገሻ አየነ ኮንፈረንሱ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ማህበረሰባዊ ለውጥና እድገት የሚያመጡ፣ ለሀገራዊ ፖሊስ ግብዓት የሚሆኑ የምርምር ጽንስ ሀሳቦች የሚፈልቁበው ኮንፈረንስ እንድሆን ተሳታፊዎችና ተመራማሪዎች የበኩላቸውን ሚና እንድወጡ አሳስበዋል። በዚህ ኮንፈረንስ ልምድ ያላቸው ተመራማሪዎች ቁልፍ ንግግሮችን ካደረጉ በኋላ ከ40 ያላነሱ የጥናት ውጤቶች ቀርበው በየዘርፋቸው ውይይት ተካሄዶባቸዋል። ይህ ውይይት ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው የጥናት ውጤቶች የተገኙበት ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ዩኒቨርሲቲው ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚገቡ ነጥቦች ጭምር የተለዩበት ነው። ዩኒቨርሲቲውን አስመልክቶ በኮንፈረንሱ የተነሱ አንዳንድ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን አስመልክተው መልስ የሰጡት የወሎ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፋሪስ ሀይሉ በዩኒቨርሲቲው ምርምርን እንደባህል ለመያዝ በወሩ መጨረሻ አርብ የምርምር ቀን በማካሄድ በየሩብ አመቱ የተመረጡ 3 (ሶስት) የምርምር ጽንስ ሀሳቦችን ለማውጣት እየሰሩ እንደሆነ ገልጸዋል። አያይዘውም ም/ፕሬዚዳንቱ እያንዳንዱ መምህር የተሻሉ ምርምሮችን ሰርቶ በታዋቂ ጆርናሎች ላይ እንድያሳትም እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል። በመጨረሻም ከ05 - 06/06/13 ዓ ም በዩኒቨርሲቲው የምርምር ኮንፈረንስ ላይ በመገኘት የምርምር ጥናቶችን ላቀረቡና ለተሳተፉ ተመራማሪዎች የላቀ ምስጋና ያቀረቡት የወሎ ዩኒቨርሲቲ የአስ/ተማሪዎች አገ/ም/ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አማረ ምትኩ ምሁራን በምርምር ላይ በማተኮር ከዓለም የቴክኖሎጅና የኢኮኖሚ እድገት ጋር የሚራመድ ማህበረሰብ የመፍጠር ታሪካዊ ሀላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል።