በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የአካዳሚክና አስተዳደር ዘርፍ የስራ ክፍሎችን የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ አካሄደ፡፡
  February 15, 2021    News

በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የአካዳሚክና አስተዳደር ዘርፍ የስራ ክፍሎችን የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ አካሄደ፡፡ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በአካዳሚክ እና አስተዳደር ዘርፍ ያሉ የተለያዩ የስራ ክፍሎችን የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል፡፡ ዛሬ በ05/06/2013 ዓ.ም በተካሄደው የስራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ በእያንዳንዱ ጽ/ቤት በመንፈቅ አመቱ የተከናወኑ ተግባራት በጥንካሬና ድክመት ተለይተው እንደቀርቡ የተደረገ ሲሆን የመፍትሄ ሃሳቦችና ቀጣይ አቅጣጫዎችም ተዳሰውበታል፡፡ በመጨረሻም የቀረበውን ሪፖርት ተከትሎ ሃሳቦች በጥያቄና መልስ እንዲንሸራሸሩ የተደረገ ሲሆን በተቋሙ ሃላፊ የማጠቃለያ ሃሳብና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ቀርቧል፡