ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለ13ኛ ጊዜ በተለያየ የሙያ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።
  July 26, 2021    News

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በሀገራችን የተከሰተውን የኮሮና ወረርሽኝ እየተከላከለ ያሰለጠናቸውን 2730 ተማሪዎች አስመርቋል። በዚህ የተማሪዎች ምርቃት መልእክት ያስተላለፉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አጸዴ ተፈራ ምሩቃን ተማሪዎች የለውጥና የሰላም አምባሳደር ሁነው እንድሰሩ አሳስበዋል። አያይዘውም ፕሬዚዳንቷ የሀገራችን የኢኮኖሚ ሁኔታ ተመራቂዎችን ለመቅጠር የሚያስችል ባለመሆኑ የመንግስት ስራ ሳይጠብቁ ስራ ፈጣሪ እንድሆኑ የበኩላቸውን ጥረት እንድወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ዩኒቨርሲቲው በደሴ ግቢ በአምስት ኮሌጆች በሁለት ት/ቤቶችና በአንድ ተቋም ሲያሰለጥናቸው የነበሩ 1781 ወንድ 949 ሴት በድምሩ 2730 ተማሪዎችን የዪኒቨርሲቲው ሴነት ሀምሌ 2/2013 ዓ ም ውጤታቸውን መርምሮ ባጸደቀው መሰረት አስመርቋል። በዚህ የምርቃ ፕሮግራም ላይ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የዋንጫና ሜዳሊያ ተሸላሚ ሁነዋል።