ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለ2013 ዓ ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች በተቋሙ ደንብና መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።
  July 26, 2021    News

የወሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በቆይታቸው ጊዜ የተቋሙን ህግና መመሪያ ተገንዝበው በህጉና መመሪያው መሰረት እንድቀሳቀሱ የሚያስችል ስልጠና አዘል ኦሬንተሽን ሰጥቷል። በዚህ ስልጠና አዘል ኦሬንቴሽን አዲስ ተማሪዎችን እንኳን ወደ ሰላም ዩኒቨርሲቲ መጣችሁ ያሉት የዩኒቨርሲቲው ተተኪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አጸዴ ተፈራ ተማሪዎች የተቋሙን ህግና መመሪያ መሰረት አድርገው በመንቀሳቀስ የመጡበትን አላማ አሳክተው እንድመለሱ አሳስበዋል። ለተማሪዎች የተሰጠው ይህ ስልጠና አዘል ኦሬንቴሽን በተቋሙ ህግና ደንብ ላይ ከማተኮሩ ባሻገር ተማሪዎች ርዕያቸውን ለማሳካት ለውጥ እንደት ማምጣት እንዳለባቸው፣ በጎ አመለካከት በምን መልኩ መያዝ እንዳለባቸው እና የእንጊሊዘኛ ቋንቋን እንደት ማሻሻል እንዳለባቸው ጭምር ነው።