በክዋኔ ኦዲት አጠቃላይ ፅንሰ ሃሳብ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ፡፡
  February 01, 2021    News

በክዋኔ ኦዴት( Performance Audit) አጠቃላይ ፅንሰ ሃሳብ፣ ዓላማ፣ አሰራርና ይዘት ዙሪያ ላይ ያተኮረ ስልጠና በደሴ ካምፓስ ከጥር 18-22/2013 ዓ.ም በደሴ ካምፓስ ተሰጠ። በወሎ ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ኦዲት አዘጋጅነት ስልጠናውን የሰጡት ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ልምድ ያላቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁር ዶ/ር አሉላ ተሰማ ሲሆኑ አዘጋጁ ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ እና መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የስልጠናው ተካፋዮች ሆነዋል። ስልጠናው በአመዛኙ የአስተዳደር ሰራተኞችን ያማከለ ሲሆን በቀጥታ የሚመለከታቸው የውስጥ ኦዲት የስራ ክፍሎችን ጨምሮ ሌሎች ከክዋኔ ኦዲት ጋር በተያያዘ ስልጠናው የሚያስፈልጋቸው የስራና የትምህርት ክፍል ፕሬዚዳንቶች፣ ፅ/ቤት ኃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል። ስልጠናው ከተለመደው የስልጠና አይነት የተለየ ነው የተባለ ሲሆን የኦዲት ፅንሰ ሃሳብ ላይ የተፃፉ ቲዮሪዎችን የማስተማር ወይም የማወያየት አይነት ስልጠና ሳይሆነ እያንዳንዱ ክፍል በተግባርና በተጨባጭ በክዋኔ ኦዲት ላይ ያሉትን ችግሮች በመዘርዘር የመፍትሄ ሃሳቦችን የሚያስቀምጥበትና የችግሮቹ ተጠያቂ ማን እንደሆነ በማስቀመጥ እርስ በርስ የተማማሩበት ስልጠና ነበር። ከስልጠናው በኋላ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/አፀደ ተፈራ እና ሁሉም ም/ፕሬዚዳንቶች በተገኙበት ስልጠናውን ለሰጡት ዶ/ር አሉላ ተሰማ እና ለሁሉም ለተሳታፊዎች የምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን እንደዚህ አይነት ስልጠናዎች ለዩኒቨርሲቲው እድገትም ሆነ በየደረጃው ላሉ ሰራተኞች የሥራ ተነሳሽነት እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ ወደፊት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስተያየቶች ተሰጥተው ስልጠናው ተጠናቋል።