የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ
  January 27, 2021    News

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በወሎ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ንግግር አደረጉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ በመገኘት ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት ዳያስፖራው ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዕድገት ባለው ሚና ላይ ንግግር አደረጉ። በዩኒቨርሲቲው ግብዣ በቦታው የተገኙት ዋና ዳይሬክተሯ ባስተላለፉት መልዕክት ኤጀንሲው ከዳያስፖራው የሚገኘውን ዕውቀት፣ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ወደ ሃገር ውስጥ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑን ገልጸው፣ ዩኒቨርሲቲዎችም በዘርፉ በዳያስፖራው ዘንድ ያለውን የካበተ ዕውቀት፣ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ለመማር ማስተማር፣ ጥናትና ምርምር እንዲሁም ማህበረሰብ አገልግሎት ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አሳስበዋል። በአውሮፓና አሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚያስተምሩ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መኖራቸውን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ፣ ሁኔታዎች ከተመቻቹላቸው ወደ ሃገራቸው ገብተው ዩኒቨርሲቲዎችን ለአጭርም ሆነ ለረዥም ጊዜ የመደገፍ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። ወሎ ዩኒቨርሲቲም በጅምር ደረጃ ያለውን የዳያስፖራ ተሳትፎ ለማሳደግ ከኤጀንሲው ጋር የጀመረውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዕምነታቸውን ገልጸዋል። ክብርት ዋና ዳይሬክተሯ በቆይታቸው ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በተጨማሪ ከደሴ ከተማ አስተዳደርና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር የተወያዩ ሲሆን፣ በዳያስፖራው ተሳትፎ በአካባቢው ሊከናወኑ በሚችሉ ዝርዝር ጉዳዮች