ወሎ ዩኒቨርሲቲ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል ከተማሪዎች ጋር ውይይት አካሄደ።
  January 14, 2021    News

በ2012 ዓ ም አጋማሽ ላይ በተከሰተ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል የወሎ ዩኒቨርሲቲ ከተማሪዎች ጋር ውይይት አካሄዷል። ውይይቱ ተማሪዎች ባላቸው አጭር የመማር ማስተማር ጊዜ ሊኖራቸው በሚገባ የሰዓት አጠቃቀም፣ የኮሮና ቫይረስ መከላከልና በተቋሙ ውስጥ ሲኖር ሊከተሉት በሚገባ ሰላም ላይ ተወያይተዋል። ተማሪዎችን በሰላም እንኳን ወደ መደበኛ የስልጠና ፕሮግራማችሁ መጣችሁ ያሉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተተኪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አጸዴ ተፈራ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኔስተር ባስቀመጠው መመሪያና ደንብ መሰረት ተማሪዎች የተቋሙን ሰላም ጠብቀው ወረርሽኙን እየተከላከሉ በተሰጣቸው አጭር የስልጠና ጊዜ ስልጠናቸውን ሊከታተሉ እንደሚገባቸው አሳስበዋል። አያይዘውም ፕሬዚዳንቷ የተለየ ተልዕኮ ተቀብሎ በተቋሙ ሰላም ላይ ችግር ለመፍጠር የሚሞክር ተማሪ ከታየ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኔስተር ባወጣው መመሪያ መሰረት ፈጣን እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ገልጸዋል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኔስተር ለከፍተኛ ትምህርት ሚኔስተር ያወጣው መመሪያና አዋጅ በህግ ት/ቤት፣ በጤና ሳይንስ እና በሳይኮሎጅ ትምህርት ክፍል መምህራን በማቅረብ ተማሪዎች እንድያውቁት ተደርጓል።