ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 25/02/2015 ዓ.ም
ለኢንስቲትዩቱ የኮሌጅ፣ የትምህርት ቤት እና የትምህርት ክፍል ሃላፊዎች በኢንጂነሪንግ እና በኮምፒዩትር ሳይንስ ዘርፍ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለውን ፕሮግራም ለመጀመር የሚያችሉ መስፈርቶችና መመዘኛዎች ዙሪያ ሙያዊ የግንዛቤ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር መላኩ ታመነ በመክፍቻ ንግግራቸው ስልጠናውን የሚያቀርቡት ፕሮፌሰር ሳሙዔል ላኬኡ በአሜሪካን አገር በማስተማር እና በምርምር የረጅም ጊዜ ልምድ ያካበቱ እና በመስኩ ከአርባ በላይ ህትመት ያላቸው መሆኑን ገልጸው ፕሮፌሰሩ ከሚያቀርቡት ሙያዊ ገለጻ ባሻገር ከሚሰሩበት ተቋም ጋር ትስስር በመፈጠር የትምህርት እድል ማመቻቸትና “Accredit” መሆን የሚችሉ ፕሮግራሞች ላይ ግንዛቤ መፍጠር የሚጠበቁ ጉዳዮች ናቸው ብለዋል፡፡
“Program Accredit” ሲደረግ ከትምህርት ጥራት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው ያሉት ዶ/ር መላኩ ይሄም የሙያ ብቃትን በማረጋገጥ የተቋሙን ደረጃ እና ተመራጭነት ከፍ ለማድረግ እንዲሁም ፕሮግራሙ የሚፈለገውን አላማ ያሳካል ወይ የሚለውን ለማረጋገጥ አይነትኛ ሚና ይጫወታል በማለት ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችንም ዳሰዋል፡፡
ፐሮፌሰር ሳሙዔል ስለ “ABET” ታሪካዊ ሁናቴ እንዲሁም “Accredit” ስለሚደረጉ ፕሮግራሞች መስፈርት እና ተያያዥ ጉዳዮች ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በነበረው ውይይትም ከተሳታፊ ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ሙያዊ ትንታኔ ሰጥተዋል፡፡