ለኢንስትቲዩቱ 5ኛ አመት የቴክስታይል ትምህርት ክፍል ተመራቂ ተማሪዎች የቅጥር እና ስራ ፈጠራ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 06/ 12/ 2014 ዓ.ም.

በየአመቱ ተማሪዎች ለምረቃ በሚቃረቡበት ወቅት እና ከዚያም ቀደም ብሎ ስለ ስራ ፈጠራ እና ቅጥር የግንዛቤ መድረክ በመፍጠር ምሩቃኑ በውድድር አሸናፊ መሆን የሚችሉበትን ስነ-ልቦና እንዲላበሱ እና በቅድመ ዝግጅት ወቅት ትኩረት የሚሰጥባቸው ተግባራት በመንቀስ ስልጠና የሚያዘጋጀው ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለ5ኛ አመት የቴክስታይል ትምህርት ክፍል ተመራቂ ተማሪዎች ተሞክሮ አዘል ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙት የቴክስታይል ትምህርት ክፍል መምህር እና የዴሊቨሮሎጂ አስተባባሪ አቶ አሮን ሙላት የስልጠናዉ ትኩረት ምሩቃን እንዴት ስራ መፈለግ እንደሚችሉ፣ የስራ ማመልከቻ እንዴት እንደሚያዘጋጁ እና በቃለ መጠይቅ ወቅት ስለሚደረግ ቅድመ ጥንቃቄ እና እንዴት ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸው ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ እንደሆነ ገለጸዋል፡፡

አቶ አሮን ከፍታ ፕሮጀክት ባዘጋጀው ስልጠና ተጠቅመው የማሰልጠን እድል እንዳገኙ በመግለጽ ስልጠናው በቀጣይም ለሌሎች የትምህርት ክፍል ተመራቂ ተማሪዎች እንደሚሰጥ አሳውቀዋል፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top