ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 08/03/2015ዓ.ም
የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ2015 ዓ.ም 1ኛ ሴሚስተር ኢንተርንሺፕ ለሚወጡ ተማሪዎች የኢንተርንሺፕ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በኢንዱስትሪ ሙያተኞች እንዲሰጥ አድርጓል::
በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠ ላይ በአከባቢው ከሚገኙ አምስት ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች የመጡ ሙያተኞች በአሰልጣኝነት ተሳትፈዋል። ስልጠናውን የሰጡት የኢንዱስትሪ ሙያተኞች ተማሪዎች በኢንተርንሺፕ ቆይታቸው የሚተገብሩ ተግባራት እና ምን ላይ ማተኮር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል::

በተጨማሪም ተማሪዎች በኢንተርንሺፕ ውጤታማ እንዲሆኑና ክህሎት ይዘው እንዲወጡ በኢንዱስትሪው ውስጥ አከባቢያቸውን በንቃት እንዲመለከቱና የሚሰሩትን ስራዎችን በእለት ፣ በሳምንት እና በወር መዝግቦ በመያዝ የኢንዱስትሪውን ምርት አመራረት፣ ጥራት እና አሰራር እንዲመረምሩ ተነግሯል።
