ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 16/01/2015 ዓ.ም
ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለኮምቦልቻ ሪጆ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር ለ2015 ዓ.ም የትምህርት በጀት አመት የሚሆን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል::
በተቋሙ ተገኝተው የድጋፍ ርክክብ ያደረጉት የኮምቦልቻ ሪጆ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የትምህርት ባለሙያ የሆኑት አቶ ጌታቸው አባተ ዩኒቨርሲቲው በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ለትምህርት ሴክተሩ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ በማስታወስ በአሁኑም ሶስት መቶ ሰላሳ ሶስት ደርዘን ደብተር እና እስክርቢቶ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል::
አቶ ጌታቸው ድጋፉ በተመረጡ ት/ቤቶች ከቀበሌ በሚላክ መረጃ መሰረት በፍትሃዊነት ተደራሽ እንደሚሆን ገልጸው አሁን ያለው የደብተር ዋጋ በጣም የናረ በመሆኑ አንድ ደርዘን ደብተር እስከ ስምንት መቶ ብር ድረስ የሚሸጥ በመሆኑ እንዲህ አይነቱ ድጋፍ የመግዛት አቅም የሌላቸው ተማሪዎች ሳይሳቀቁ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እገዛ ያደርጋል ብለዋል::
አገር የሚገነባው በትምህርት ነው ያሉት የትምህርት ባለሙያው ዩኒቨርሲቲው ላበረከተው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ምስጋና ችረው አብሮ ለመስራት ሁለንተናዊ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መልእክት አስተላልፈዋል::
ከተቋሙ ባገኝነው መረጃ መሰረት ለደብተር እና እስክርቢቶ ከሁለት መቶ ሽህ ብር በላይ ወጭ እንደተደረገ ማወቅ ተችሏል::