ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 28/02/2015 አ.ም።
በስልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ም/ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሀብታሙ መሃመድ ስልጠናው ካለው ፋይዳ አኳያ ተሳታፊዎች በትኩረት በመከታተል በመረጃ አያያዝና አስተዳደር፣ አገልግሎት አሰጣጥ እና ደንበኛ አያያዝ ዙሪያ በስራቸው ተጨባጭ ለውጥ ሊያስመዘግቡ እንደሚገባ ገልጸዋል::
በኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ የኢንፎርሜሽን ሲስተም መምህርና ተባባሪ ሬጄስተራር አቶ መከተ ተድላው ስልጠናው በዲጂታል ሊደርሽፕ እና ደንበኛ አገልግሎት ዙሪያ እንደተሰጠ በመግልጽ አላማውም ባለሙያዎች በአመለካከት፣ በአስተሳሰብ እና በክህሎት የዳበረ ማንነትን ይዘው ዘመኑ የወለዳቸውን ቴክኖሎጂዎችና አሰራሮችን በመጠቀም የደንበኛ ርካታን ማረጋገጥ ነው ብለዋል::
አቶ መከተ ከስልጠናው በኋላ ባለሙያዎች በቀሰሙት እንዲሁም በራስ ተነሳሽነትና ጥረት ጭምር ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት ገጽታ መገንባት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው ብለዋል::
በወሎ ዩኒቨርሲቲ በስብእና ግንባታ እና ስራ እድል ፈጠራ ላይ የረጅም ጊዜ የማሰልጠን ልምድ ያላቸው መምህራን በሰጡት በዚህ ስልጠና መባቻ ላይ አስተያየት የሰነዘሩት ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለአሰልጣኞች ምስጋና አቅርበው በሁለት ቀን የተሰጠው ስልጠና ትልቅ መነቃቃት እንደፈጠረላቸው በመግለጽ ስልጠናው የግል ስብእናን እና የአእምሮ ውቅርን በመፈተሽ ጥረታችንን እንድናሳድግ ተነሳሽነትን የሚፈጥር በመሆኑ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል የሚል ሃሳብ ሰንዝረዋል::