ህዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም (ወዩ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጽ/ቤት)
ዛሬ ህዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም በኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት በምህንድስና የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 1062 ወንዶች እና 332 ሴቶች በድምሩ 1394 ተማሪዎችን በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግር በማስመረቅ ላይ ይገኛል።
በእለቱ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የተከበሩ ዶ/ር አህመዲን መሃመድ፣ የዩኒቨርሲቲያችን የቦርድ አባላት፣ የዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የሴኔት አባላትና መምህራን ተገኝተዋል።

በምረቃ ሥነስርዓቱ ላይ የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር መላኩ ታመነ የስራ ሪፖርት አቅርበዋል። የወሎ ዩኑቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነም የእኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የዕለተ የክብር እንግዳ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የተከበሩ ዶ/ር አህመዲን መሃመድ ለተመራቂ ተማሪዎች የስራ መመሪያ አስተላልፈዋል። በንግግራቸውም “ይቺን በደምና በአጥንት የተከበረች ሃገር በላብና በድካም ጠብቃችሁ እንዲታቆዩዋት” ብለዋል።
ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን። መልካም የስራ ዘመን እንድገጥማችሁም እንመኛለን።
