የግዕዝ ትምህርት ክፍል በግዕዝ ቋንቋ የቅኔና የስነ ጽሁፍ ዝግጅት አካሄደ።

የካቲት 13/2016 ዓ ም (ወዩ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጽ/ቤት)

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የግዕዝ ትምህርት ክፍል የግዕዝ ቋንቋን ለማበልጸግ በግዕዝ ቋንቋ የቅኔና የስነ ጽሁፍ ዝግጅት አካሄዷል።

በዚህ ዝግጅት ላይ የተገኙት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ጥንታዊ እና ዘመናዊ የኢትዮጵያን ትምህርትና ሳይንስን ለመመርመር የግዕዝ ቋንቋንንና አረብኛን መመርመርና ማበልጸግ ተገቢ በመሆኑ ወሎ ዩኒቨርሲቲ በቋንቋዎች ላይ የጀመረውን እንቅስቃሴ በትኩረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

አያይዘውም ፕሬዚዳንቱ የግዕዝ ቋንቋን ለማጽናት የግዕዝ ቋንቋ ተቋምን በተገቢው ለማደራጀት ጥረት እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል።

የግዕዝ ትምህርት ክፍል ባዘጋጀው የቅኔና የስነ ጽሁፍ ዝግጅት ላይ በመምህራንና ተማሪዎች ቅኔ፣ ስነ ጽሁፍና ተውኔት በግዕዝና አማርኛ ቋንቋዎች የቀረቡ ሲሆን በግእዝ ቋንቋ በተማሪዎች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሂዷል።

በዝግጅቱም የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጅ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት ሃዋ ወሌ (ዶ/ር) ፣ የማህበራዊና ሰብአዊ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር አለመጣ አሰፋን ጨምሮ የግእዝ ትምህርት ክፍል መምህራን፣ ተማሪዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዦች እንግዶች ታድመዋል።

Scroll to Top